ኣንደበተ-ርቱእኣዊ ኣነጋገሮች (ክፍል ፪)፦ “ስሜ እከሌ ማንትስ እባል ኣለሁ” ወይስ “ስሜ እከሌ ማንትስ ነው”?

16
2262

በ ልዑል ካሕሳይ

በክፍል ፩ መጣጥፌ ““ስምዎ ማን ነው?” ወይስ “ስምዎ ምንድን ነው?””፣ ቃሉ ‘ምን’ ግለሰዎችን እንጂ ስሞችን ተደራሽ ማድረጊያ እንደ ኣልሆነ ወይም ሊሆን እንደ የማይገባው ለማስረዳት ሞክሬ ኣለሁ። በዚህ ሁለተኛ ክፍል መጣጥፌ ደግሞ፣ ከስም ጋር በተገናኘ የኣስተዋልሁትን በመጠኑ ለየት ያለ ችግር ኣቀርባለሁ። በዚህ መጣጥፌ ርዕስ ውስጥ የጠቀስኩት ህጸጻዊ ኣነጋገር ብዙ ጊዜ የሚስተዋል ሰዎች ራሳቸውን በመገናኛ ብዙሓን ሲያስተዋውቁ ነው። “ስሜ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” ወይም “ስሜ ኣስቴር እባል ኣለሁ” ኣይነት ኣባባሎች እየተለመዱ የመጡ ይመስላል።

በቅርቡ በኣንድ የመገናኛ-ብዙሓን ኣውድ ላይ ኣንድ እንግዳ ራሳቸውን “ስሜ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” (እውነተኛ ስማቸውን ቀይሬው ኣለሁ) በማለት እንደ ኣስተዋወቁ ኣስተዋልሁ። ይህ ኣነጋገር ከስዋስው ኣንጻር ስህተት ነው። እንዲያውም ኣረፍተ-ነገሩ ሁለት ስዋስዋዊ ህጸጾችን የኣጣመረ ነው። የመጀመሪያው እና ቀለል ያለው ህጸጽ ከቃሉ ‘ስሜ (ስም)’ ጋር ቃሉ ‘እባል (መባል)’ ኣብሮ መቅረቡ ነው። የቃሉ ‘ስም’ ትርጉም ‘መባል’ ን ያካትታል። ኣንድ ሰው ወይም ኣንድ ነገር የሆነ ነገር ከተባለ ወይም በሆነ ነገር ከተጠራ፣ በዛ በተባለበት ወይም በተጠራበት ነገር ስያሜ ኣግኝቶ ኣል። በመሆኑም፣ የሁለቱ ቃላት ኣብሮ መገኘት ስዋስዋዊ ሰነፍ-ድግግሞሽን ይፈጥራል። በመሰረቱ ‘ኣበበ ከበደ’ የእኔ ስም ነው እንጂ የስሜ ስም ኣይደለም። በሌላ ኣባባል፣ ኣበበ ከበደ ራሱ ስሜ ነው። በመሆኑም፣ ትክክለኛው ኣባባል “ስሜ ኣበበ ከበደ ነው” ኣሊያም “እኔ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” ነው።

ሌላው እና ከስዋስው ኣንጻር የከበደው ህጸጽ ኣረፍተ-ነገሩ በ ፫ኛ ወገን ቃሉ ‘ስሜ’ ተጀምሮ በ ፩ኛ ወገን ቃላቱ “እባል ኣለሁ” መገባደዱ ነው። ‘ስሜ’ ማለት ‘የእኔ ስም’ ሲሆን፣ የኣረፍተ-ነገሩ ሳቢ ‘እኔ’ ሳይሆን ‘ስም’ ነው። ‘ስም’ ደግሞ ግዑዝ ስለ ሆነ ፫ኛ ወገን ነው። ‘እባል ኣለሁ’ ውስጥ የተካተተው ስውር ተውላጠስም ‘እኔ’ ሲሆን፣ ስዋስዋዊ ፩ኛ ወገን ነው። እንደ የምናውቀው የ፩ኛ ወገን ውስጥ የሚካተቱት ተውላጠስሞች “እኔ” እና “እኛ” ሲሆኑ፤ በ ፫ኛ ወገን ውስጥ የሚካተቱት ተውላጠስሞች ደግሞ “እርሱ”፣ “እርሷ”፣ “እርሳቸው”፣ እና “እነርሱ” ናቸው።

ቃሉ ‘ስሜ’ ልክ እንደ ቃላቱ ‘ቤቴ’፣ ‘ብዕሬ’፣ ‘ልብሴ’፣ ወዘተ እና እንደ ማንኛቸውም ሌሎች ግዑዛን ነገሮች የሚመደበው በ ፫ኛ ወገንነት ነው። ከስዋስው ኣንጻር ‘እኔ’ ከ ‘ስሜ’ የተለየሁ ስብዕና ያለኝ ፍጡር ነኝ። ስሜን ልቀይረው እችል ኣለሁ፣ እኔን ግን መቀየር ኣልችልም። ስለዚህ ስሜ እና እኔ የተለያየን ነገሮች ነን። ስለ ስሜ ሳወራ፣ ልክ ስለ ስልኬ ወይም ስለ ጫማዬ እንደ የማወራ፣ ከራሴ ለይቼ ነው የማወራ።

ለምሳሌ፣ “ጫማዬ ቆንጆ ነው” እንጂ “ጫማዬ ቆንጆ ነኝ” ማለት ኣልችልም። በተመሳሳይ፣ “ስልኬ ኣይ-ፎን ይባል ኣል” እንጂ “ስልኬ ኣይ-ፎን እባል ኣለሁ” ማለት ኣልችልም። በመሆኑም “እኔ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” ማለት እችል ኣለሁ እንጂ “ስሜ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” ማለት ኣልችልም–እኔ እና ስሜ የተለያየን ነገሮች ስለ ሆን።

“ስምን መልኣክ ያወጣዋል” እንዲሉ፣ ኣንድ-ኣንድ ሰዎች ለስማቸው ካላቸው ኣክብሮት የተነሳ፣ ወይም ራሳቸውን ከስማቸው ለይተው ለማየት ከመቸገር የተነሳ ይህን ሃሳብ ይቃወሙ ይሆን ኣል። እንዲያውም ይህ ስዋስዊ ችግር የበለጠ የሚጎላ ሰዎች ስለ የራሳቸው የኣካል ክፍሎች ሲያወሩ ነው። ለምሳሌም ኣረፍተ-ነገሩን “እጄን ኣመመኝ” ያስተውሉ ኣል። ትክክለኛው ኣባባል “እጄ ታሞ ኣል” ነው። ከስዋስው ኣንጻር፣ ምንም እንኳን እጄ የእኔ ቢሆንም፣ እጄ እኔ ኣይደለም። የሚቀጥለው ኣረፍተ-ነገር በእጄ እና በእኔነቴ መካከል ያለውን ስዋስዋዊ ልዩነት በትክክል ያሳያል፦ “እጄ ሰፊ ነው።” “እጄ ሰፊ ነኝ” እንደ የማይባል ይመልከቱ ኣል። ይህም ‘እጄ’ ስዋስዋዊ ፫ኛ ወገን መሆኑን እና ከስዋስዋዊው ፩ኛ ወገን ከ ‘እኔ’ የተለየ መሆኑን ያመለክታል።

እየ ኣንድ-ኣንዱ ኣረፍተ-ነገር የራሱ ሳቢ ኣለው። በኣንድ ኣረፍተ-ነገር ውስጥ ሳቢ የሚለይ ድርጊት ፈጻሚ በመሆኑ፣ ድርጊት ፈጻሚ ከኣል ሆነ ደግሞ ስለ እርሱ የተነገረ ነገር በመኖሩ ነው። በየኣማርኛ ስዋስው ሕግ መሰረት፣ የሳቢው እና ግሱ በየሚያመላክቱት ተውላጠስም መጣጣም ኣለባቸው። ለምሳሌ፣ ኣንጋፋውን ኣረፍተ-ነገር ‘ኣበበ ዳቦ በላ’ ያስተውሉ ኣል። በዚህ ኣረፍተ-ነገር ውስጥ ሳቢው ‘ኣበበ’ ሲሆን የሚያመላክተው ስዋስዋዊ ተውላጠስም ‘እርሱ’ ነው። በተመሳሳይ፣ ግሱ ‘በላ’ ሲሆን፣ የሚያመላክተው ተውላጠስም ‘እርሱ’ ነው። “ኣልማዝ ዳቦ በላ” ወይም “ኣበበ ዳቦ በላች” ወይም “ኣልማዝ እና ኣበበ ዳቦ በላ” ካልን ግን ሳቢው እና ግሱ የሚያመላክቱ ኣቸው ተውላጠስሞች ስለ የሚለያዩ ስዋስዋዊ ችግር ይከሰታል ማለት ነው።

“ስሜ ኣበበ ከበደ እባል ኣለሁ” ካልን ሳቢው እና ግሱ የሚያመላክቱ ኣቸው ተውላጠስሞች ላይጣጣሙ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም፣ ከላይ እንደ ጠቀስሁት፣ ‘ስሜ’ ማለት ‘የእኔ ስም’ ሲሆን፣ ልክ እንደ ‘የእኔ ተሽከርካሪ’፣ ተውላጠስሙ ‘እርሱ’ ሲሆን፣ ‘እባል ኣለሁ’ ግን የሚያንጸባርቁት ተውላጠስም ‘እኔ’ ነው።

በክፍል ኣንድ መጣጥፌ ማገባደጃ ላይ ለመግለጽ እንደ ሞከርሁ፣ እንደ እነዚህ ኣይነት ህጸጾች ኣሁን ካለንበት ማሕበረ-ምጣኔሃብታዊ ሁኔታ ኣንጻር ግዙፍ መስለው ኣይታዩ ይሆን ኣል፣ ነገር ግን የቋንቋ ኣጠቃቀማችን ያለበትን ኣሳሳቢ ደርጃ ኣመላካች ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ እድገት ወሳኝ የሆነውን ስልጠታዊ መግባቢያ እንድ ኣናዳብር የሚከለክሉ ጋሬጣዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የቋንቋ ኣጠቃቀም ቀውስ እንደ ኣለ የማምን ስሆን፣ የሚከተሉት የቀውሱ ማመላከቻዎች ሃገራችን ወደ ረቀቀ ማህበራዊ እና ምጣኔሃብታዊ እድገት እንድ ኣትደርስ ማድረግ ኣቸው ኣይቀሬ ነው፦

 • ሃገራዊ ቋንቋዎች ለታላላቅ ሳይንሳዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ኣጠቃቀሞች እንዲ በቁ ኣለመዳበራቸው

 • የእንግሊዝኛ ቃላት በድንገት ቋንቋ ኣችንን መውረራቸው እና በዚህም ምክንያት የተከሰቱ በርካታ ችግሮች (ከስዋስው ብልሽትና ከመግባባት እንቅፋት በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ በኣለው የመልካም ኣስተዳደር እጥረት ላይ የሚያስከትለው ተጨማሪ ጫና)

 • መንግስት የባእድ ቋንቋን በሃገሪቱ ውስጥ የመማሪያ መሳሪያ መሆኑን መኣቆም ኣለመቻሉ

 • ትልልቅ ሃግራዊ ተቋማት እና ታላላቅ መሪዎች ሳይቀሩ በኣልተማረው ሕዝብ ጫንቃ ላይ ከሞላጎደል እንግሊዝኛን በጉዲፈቻ ማዳበላቸው፣

 • ዜጎች ኣንደበታቸውን በፈቱበት ቋንቋ ሃሳባቸውን በጥራት እና በፍጥነት መግለጽ ኣለመቻላቸው፣ ሰዎች ባዶ ቃላትን (“እንትን”) በንግግሮቻቸው ውስጥ ኣብዝተው መጠቀማቸው፣

 • ዜጎች በገዛ ሃገራቸው የባዕድ ቋንቋ ባለመቻላቸው የሚከሰተው ኣለመግባባት እና የመልካም ኣስተዳደር እጥረት (ለምሳሌ፣ በሃኪሞች እና በተለይም የእንግሊዝኛ ቃላትን በማያውቁ ህመምተኞች መካከል መግባባት ኣለመቻሉ)

በሌላ መጣጥፍ እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ።

16 COMMENTS

  • looser tribalist, the one like you are the next ISIS bombers.Dividing the people day and night and spreading trial hate.While enjoying the freedom of the west, you propagate hate. You might think you are invisible behind your pc but you are not! Hate and fake news is a crime everywhere!

 1. Aniger,
  We know you are in the business of denial the truths and promoting TPLF propaganda!!
  Since I know where you stand, I won’t even bother to open the link you are suggesting — Ethiopians be careful! It could be a virus!!!

  • SHINTAM! Tell your story to your kids and your wife. Looser! It is better to let your family read your comments at nazerth and I am sure they will definitely proud of you.

   • bean brain,
    Ante niftam soulless molacha laeba Woyane!! SO WHAT IF SOMEONE IS SHINTAM? Nothing is worse in this world than being mass looters and mass murderers like you remorseless bloody hand woyanes!!

  • hope less HOPE ,

   SORRY FOR EXPOSING U .YOUR FAKE NEWS WERE DOMINANT MONTHS AGO .NOW , TRUTH IS BEING SERVED .

   PEOPLE NEED TO = CRITICISE WEAKNESS AND APPERECIAT STRENGTH .

   DOOMS DAY CALLERS have no place in Ethiopia today

 2. ውድ ወንድሜ ልዑል ካሕሳይ፣
  “ኣንደበተ-ርቱእኣዊ ኣነጋገሮች”ህ በጭስ ከታፈነ ቤት ውስጥ ወጣ ብሎ ንጹሕ አየር የመቀበልን ያህል አስደስተውኛል። እግዜር ይስጥልኝ። አንድ ተማሪ አፍርተሃልና ቀጥልበት።

 3. ወዳጄ – ቋንቋችን በተመለከተ በሁለት ክፍል ያቀረብከው ለእኔ ይመቸኛል። አዎን የወያኔ ትልቁ ሴራ ቋንቋችንን መደባለቅ ነው። ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት ሃገር ሆናለች። ሰው በሚችለው አማርኛን መናገሩ የሚደነቅ ነገር ነው። ፍትህ በለሌበት ምድር፤ ጠበንጃ ያነገቱ የአንድ ጎሳ ጥርቅሞች ያዘው ጥለፈው በማለት ህዝባችንን በሚያሳድድበት የወያኔ ስርዓት ሰው ድዳ አለመሆኑም የሚያስገርም ነው።
  በመሰረቱ አማርኛ ቋንቋ ለሚናገረውና ሰምቶ ለሚረዳው የልብን የሚያደርስ ቋንቋ ነው። እርስዎ እንዳሉት የአጻጻፍ፤ የአነጋገር ህግጋትም አለው። የሚያኮራ ቋንቋ ነው። ታዲያ የዛሬዎቹ ሙታን ፓለቲከኞች ሃገር በቀል ነገርን ጠልተው የባህር ማዶውን ፊደላት ለመገልገል ባደረጉት ሙከራ እዚህ ገባ የማይባል አሳር ውስጥ ህዝባችንን ከተውታል። ሰው ሃሳቡን በግጥም፤ በቅኔ፤ በተረትና ምሳሌ በሌላም አባባል የአማርኛ ቋንቋን ይገለገልበታል። በመሰረቱ ቋንቋ መግባቢያ ነው። በአለም ላይ ጨቋኝ ቋንቋ ካለ እንግሊዝኛ ብቻ ነው (ቧልት)። ከሥር ያለውን ግጥም እንመልከት።

  ከረምት ገባ እያሉ እያስፈራሩኝ፤ ምን አባቴ ላድርግ እስኪ እንዲሞቀኝ
  እርጥቡን ደረቁን አንድ ላይ አስሬ እሳት ላይ ብጥለው
  ሞቀቱ ቀረና ጢስ ቤቴን አፈነው።
  ጋቢውን እንዳልል አይደርስልኝ ቶሎ፤ ብርድልብስ ለመግዛት ገንዘቡ የለኝም
  እሳቱ እምቢኝ ካለ፤ ጋቢው ብርድልብሱ ዛሬ ካለተገኘ
  ሙቀቴን ፈልጓት ከምትገኝበት
  ቋንቋየ ቋንቋሽ ነው አይጠፋሽም ስፍራው
  ንግግር አያሻም ሙቆ ለመሟሟቅ
  ዳበስ ዳበስ አርጊው የሰራ አከላቴን
  የእኔ ገላ ግሎ አንቺንም እንዲያሞቅ
  እኔ እስዋን ሳሞቃት እስዋ እኔን ስታግል
  ያ ክረምት አለፈ እንደተቃቀፍን።
  ደራሲው፡ተስፋ በጊዜው
  የጎዳና ቀልደኛው እንዳለው ” አይ አማርኛ እንደ አበጁሽ ትበጃለሽ” ነው። አማርኛ ማለፊያ ቋንቋ ነው። ተመስገን ነው ወያኔ ተናዶ ቋንቋውን አባይ ውስጥ ጥሎት ግብጽ ላይ አለመገኘቱ!

  • TESFA ,

   why do you hate it when others use their language in EDIR , EQUB , SCHOOL, MARKET , JUDICIARY etc .

   BECAUSE , the will not listen to your narrative , fake history ?

   INFLUENCING OTHERS AND DOMINATING THEM USING LANGUAGE AS A TOOL IS DEAD AND BURIED .

   what we need to do now is PROMOTE DEMOCRATIC NATIONALISM .People who are proud of their language and identity BUT accept others as equals and brothers .

   MY WAY OR HIGH WAY is a past belief .

   I AM PROUD WHEN I HERE PEOPLE IN ADDIS speaking mixed language WOLAYTA , TIGRINA , GURAGE ,KUBE

   I like it so much .MELTING POT !

   • Dear Nana,
    How much do you get paid by the TPLF to diffuse and confuse what is clear to everyone, except to a few pinheads like you? At no point, I belittle anyone’s language or culture. What I wrote is strictly about the Amharic language. Your borrowed terminology of “Melting pot” does not exist anywhere in the world anymore. Rather, it is becoming a salad bowl. Have a taste and get your fill. It may cure your moronic point of view.

    • TESFA = do you think every one who oppose your rotten old mentality is paid ?

     yes I AM PAID = My country’s peace , development and change in my peoples’ condition of life IS BIG PAYMENT TO ME .
     I FEEL I AM A MILLIONAIRE !
     ==========================

     Psychopathic/sociopathic BEHAVIOUR OF TOXIC ILLITARATE DIASPORA

     You may have heard people call someone else a “psychopath” or a “sociopath.” But what do those words really mean?

     You won’t find the definitions in mental health’s official handbook, the Diagnostic and Statistical Manual of Mental Disorders. Doctors don’t officially diagnose people as psychopaths or sociopaths. They use a different term instead: antisocial personality disorder.

     Most experts believe psychopaths and sociopaths share a similar set of traits. People like this have a poor inner sense of right and wrong. They also can’t seem to understand or share another person’s feelings. But there are some differences, too.

     Do They Have a Conscience?

     A key difference between a psychopath and a sociopath is whether he has a conscience, the little voice inside that lets us know when we’re doing something wrong, says L. Michael Tompkins, EdD. He’s a psychologist at the Sacramento County Mental Health Treatment Center.

     A psychopath doesn’t have a conscience. If he lies to you so he can steal your money, he won’t feel any moral qualms, though he may pretend to. He may observe others and then act the way they do so he’s not “found out,” Tompkins says.

     A sociopath typically has a conscience, but it’s weak. He may know that taking your money is wrong, and he might feel some guilt or remorse, but that won’t stop his behavior.

     Both lack empathy, the ability to stand in someone else’s shoes and understand how they feel. But a psychopath has less regard for others, says Aaron Kipnis, PhD, author of The Midas Complex. Someone with this personality type sees others as objects he can use for his own benefit.

 4. ONE LANGUAGE , ONE RELIGION etc

  a FEUDAL MOTTO to control others .
  many language , many religions , many beliefs, many choices BUT ONE PEOPLE .UNITY IN DIVERSITY .

  IF U WANT TO GO TO ANOTHER PLACE , LEARN THEIR LANGUAGE .DO NOT EXPECT ALL TO STUDY YOUR LANGUAGE !

  FEUDALS headache ========WHY DO NOT PEOPLE LISTEN TO ME ? WHY DO NOT THEY ACT BASED ON MY TALK ? WHY DO PEOPLE USE THEIR MIND ?WHY DO PEOPLE ESCAPE MY CONTROL ?

  MELES WAS GUINES .HE PULL THE RUG UNDER THE FEET OF FEUDALS .PEACE BE UPON HIM!

  YOU WORRY ABOUT AMHARIC (YOUR LANGUAGE ), OTHERS WILL WORRY ABOUT THEIR OWN LANGUAGE !

Comments are closed.